የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ከጀርመን የልማት ድርጅት (GIZ) ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ከጀርመን የልማት ድርጅት (GIZ) ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡ የካቲት 2015 ዓ.ም. የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ ከጀርመን የልማት ደርጅት(GIZ) ተወካዮች ጋር በኢነርጂ ልማት ትብብር ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ የኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነት እድሜ ያስቆጠረ ግንኙነት መሆኑን አውስተው በተለይ፤ የጀርመን የልማት ድርጅት በኢነርጂ ልማት ዘርፍና በሌሎች መስኮች አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው አክለውም በኢትዮጵያ የታዳሽ ሀይል የማመንጨት አቅም ከፍተኛ ቢሆንም እንደሀገር የሀይል አቅርቦት ዝቅተኛ መሆኑንና የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ የአጋር ደርጅቶች ሚና ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይ በኢትጵያ የሀይል ማመንጫ ኢንቨስትመንት፣ የግሉን ዘርፍ ጨምሮ የኢነርጂ ሴክተሩን አቅም ማጎልበት፣ ገጠራማውን የኢትዮጵያ ህዝብ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ፣ አነስተኛ የሀይድሮ ፓወርን ማስፋፋት፣ በገጠር አካባቢ ንጹህና ተሻሽለው የቀረቡ የምግብ ማብሰያ ሀይልን ማስፋፋት እና ውጤታማ የሆነ የሀይል አጠቃቀምን ማሳደግ ላይ አብሮ መስራት እንደሚያስፈግ ገልጸዋል፡፡ የጀርመን የልማት ድርጅት (GIZ) ተወካይ ሚ/ር አሌክሳንደር ሃክ በበኩላቸው ተቋማቸው በኢነርጂ ልማት ዘርፍ እያደረገ የሚገኘውን ድጋፍ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ጀርመን የሁለትዮሽ ትብብር በGIZ በኩል ከፈረንጆቹ 1964 ጀምሮ ቴክኒካል ድጋፍ በማድረግ በግሉ ዘርፍ፣ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪውና የኢነርጂ ዘርፉን በመደገፍ በርካታ ስራ እየሰራ እየሰራ ይገኛል፡፡

Share this Post