የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከGIZ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ሴት መሀንዲሶች ስልጠና ሰጠ።
የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር በክልሎች ለሚገኙ ሴት የኢነርጂ ባለሙያዎች በሶላር ዝርጋታና ጥገና ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።
ለሰልጣኞች በቦታው በመገኘት ሰርተፍኬት የሰጡት የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ሀገራችን የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማሳደግ እና ዜጎችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ ሲሆን ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የሰው ሀይል እጥረት እንዳይኖርና በተለይ በአዲሱ የኢነርጂ ፖሊሲ ሴቶች ወጣቶችና አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን ተሳታፊ ለማድረግ፤ በገጠር አካባቢ ለሚካሄደው የሶላር ኢነርጂ ማስፋፋት ስራ ላይ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በመሆኑም ሴቶችን አሰልጥኖ ብቁ በማድረግ በቀጣይ በሀይል ስርጭት ላይ በግሉ ዘርፍ ተሳታፊ እንዲሆኑና የኤሌክትሪክ ህብረት ማህበራትን በማቋቋም ግንባር ቀደም ማድረግ የሁላችንም ሀላፊነት ነው ብለዋል፡፡
የጂአይዜድ ተወካይና የስልጠናው አስተባባሪ ኢንጂነር ፌቨን በቀለ በበኩላቸው ስልጠናው ሴቶችን በማብቃት በሚንቀሳቀሱበት አካባቢ የሚያጋጥማቸውን ችግር እራሳቸው ለመፍታት በተለይ በሶላር ኢነርጂ ብቁ ባለሙያ እዲሆኑ ማድረግ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ይህ ስልጠና ለመጀመሪያ ጊዜ ቢሆንም ከሰለጠንን ቡሀላ ወደ ስራ በምንገባበት ወቅት በተለይ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ስራችን ውጤታማ እንዲሆን ሊያግዘን ይገባል ብለዋል ስልጠናው በዚህ ሳያቆም ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡
ስልጠናው በሁለት ዙር የሚሰጥና በሶላር ኢነርጂ ዝርጋታና ጥገና ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን በመጀመሪያ ዙር ከኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ ሀረሪ፣ ጋምቤላ፣ እውን (የኢትዮጵያ ሴቶች ኢነርጂ ባለሙያ) እና ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለተውጣጡ ሴት ኢንጅነሮች ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን በዚህ ዙር የወሰዱት ሴት ሰልጣኞች በጀኔራር ሶላር ፒቪ ላይ የንድፈሀሳና የተግባር ስልጠና የወሰዱ ሲሆን፤ ስልጠናው የ5 ቀናት ቆይታ እንደነበረው ተገልጿል ፡፡