የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ5 ወራት የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።
ታህሳስ 06፣ 2015 ዓ.ም. የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከክልል የውሃና ኢነርጂ ቢሮዎች ጋር በመሆን የ5 ወራት የፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ገምግሟል።
በበይነመረብ በተካሄደው ውይይት የአማራ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ፤ የቤንሻንጉል ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ፤ የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል
ውሃ፣ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ እና የደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል የውሃ፣ መስኖና ማዕድን ቢሮ በኩል የፕሮጀክት አፈጻጻም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በውይይት ወቅትም ከኮንትራክተሮች ፣ ከሲሚንቶ አቅርቦት አንጻር፣ ከውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ጋር በተያያዘ፤ የፕሮጀክት ጨረታ አሳታፊነትና ግልጸኝነትን በተመለከተ ውይይት ተደርጓል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ሲያጠቃልሉ እንደገለጹት የሚታዩትን ተግዳሮቶች ለመፍታት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ የመፍትሄ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ገልጸው በቢሮዎቹ በኩልም ተገቢው ጥረት መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል።
በመጠናቀቅ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ላይ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ፤ ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች በጥናት ተለይተው እንዲቀርቡ፤ አሳታፊነት ትኩረት እንዲሰጠው አቅጣጫ ተቀምጧል።