ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከ423 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የመስክ ተሸከርካሪዎችን አከፋፈለ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዋጋቸው ከ423 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የመስክ ተሸከርካሪዎችን ለክልሎች አከፋፈለ ፡፡ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዋጋቸው ከ423 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 69 የመስክ ተሸከርካሪዎችን በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ በተካሄደ የርክክብ ፕሮግራም ላይ ለክልሎች አከፋፈለ፡፡ በርክክብ መርሃግብሩ ላይ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ እንደገለጹት ዛሬ ርክክብ የሚፈጸምባቸው የመስክ ተሸከርካሪዎች በየክልሎቹ ውሃ፣ ጤናና ትምህርት ቢሮዎች በአንድ ቋት መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራም ለሚገነቡ ተቋማት ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ ታሳቢ የተደረገ ነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም ተሸከርካሪዎቹ የክልሎችን አቅም ለማጠናከር በሁለተኛው ምእራፍ የአንድ ቋት መጠጥ ውሃ ሳኒቴሽንና ሀይጂን ፕሮግራም የተገዙ መሆናቸውን ተናግረው ለክልል ተወካዮች የቁልፍ ርክክብ አድርገዋል፡፡ በሁለተኛው የከተሞች መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራም በሀገራችን በሁሉም ክልሎችና በ355 ወረዳዎች እየተተገበረ ያለ ሲሆን ይህን ሥራ በስፋትና በይበልጥ ለማሳደግና ለማስፋፋት እንዲያግዝ የፌዴራል ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለፌዴራል እና ለክልል ዋሽ ፈፃሚ አካላትና ከክልል እስከ ወረዳ ላሉ ለዘርፉ ባለሙያዎች የተለያዩ የአቅም ግንባታ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ ቀደም የወረዳ ውሃና ኢነርጂ፣ የጤና እና የትምህርት ጽ/ቤቶች ያላቸውን የሎጂስቲክስ ችግር በመቅረፍ ማህበረሰቡ ቀጣይና ተከታታይ የውሃ አቅርቦትና የሳኒቴሽን አገልግሎት ማግኘት እንዲችል ታስቦ በተመሳሳይ ለዚሁ ስራ ማስፈፀሚያ የሚሆኑ 510 ሞተርሳይክሎች ለየክልሎች እንዲሰራጭ መደረጉ ይታወሳል፡፡

Share this Post