ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በጅግጅጋ ከተማ የተገነባው የሜትሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል ህንፃ ተመረቀ።

ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በጅግጅጋ ከተማ የተገነባው የሜትሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል ህንፃ ተመረቀ።

ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የሶማሌና አጎራባች ክልሎች የሜትሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል ህንፃ ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል።

የፌደራል የዉሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ እና የኢትዮጲያ የሜትሮሎጂ ኢኒስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባዉን የሶማሌና አጎራባች ክልሎች የሜትሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል ህንፃ መርቀዉ ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

የህንፃዉ ግንባታ በስምንት ወር ጊዜ ዉስጥ ተጠናቆ ለምርቃት መብቃቱ ተገልጿል።

በዚህ ወቅት የፌደራል የዉሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ የሶማሌና አጎራባች ክልሎች የሜትሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል የተገነባዉ ህንፃ ለምርቃት መብቃቱ ለአከባቢዉ ህብረተሰብ የተጠናከረ የሜትሮሎጂ አገልግሎቶችን ለመስጠት ያስችላል ብለዋል ።

የኢትዮጲያ የሜትሮሎጂ ኢኒስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ በበኩላቸዉ ኢኒስቲቲዩቱ በሀገሪቱ ባሉት 11 ማእከላት አማካኝነት ለህብረተሰቡና ባለድርሻ አካላት ወቅታዊ የሜትሮሎጂ አገልግሎቶችን ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የህንፃዉ ግንባታ በስምንት ወር ወስጥ መጠናቀቁ እንደሀገር የፕሮጀክት የመፈፀም አቅምን እያደገ መምጣቱን ያሳያል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ለምርቃት የበቃዉ ህንፃ ማዕከሉ በሶማሌ ክልልና በአጎራባች አከባቢዎች የሚሰጣቸዉን የሜትሮሎጂ አገልግሎቶችን ያጠናክረዋል ብለዋል።

የሶማሌና አጎራባች ክልሎች የሜትሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል የህንፃ ምርቃት ስነሰርአት ላይ የፌደራል ፤ የሶማሌና አጎራባች ክልሎች የተለያዩ የስራ ሀላፊዎችም ተገኝተዋል።

Share this Post