ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልል ውሀና ኢነርጂ ቢሮዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የ2016ዓ.ም. በጀት ዓመት የስድስት ወር እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እያደረገ ነው፡፡

የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልል ውሀና ኢነርጂ ቢሮዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የ2016ዓ.ም. በጀት ዓመት የስድስት ወር እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እያደረገ ነው፡፡

ጥር/2016 ዓ.ም(ው.ኢ.ሚ) መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እቅድ የክልሎች እቅድ መሆኑን ገልጸው፤ የሚኒስትሪው አፈጻጸም የክልሎችን እንደሚገልጽና የክልሎች ጥንካሬ የተቋሙ ስኬት ይሆናል ብለዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ በሚያከናውናቸው ሶሰቱ ዘርፎች ባለፉት አመታት የተሻለ ስራ የተሰራበት ሁኔታ መኖሩን ገልጸው፤ ከወቅታዊ ሁኔታዎች አንጻር ያመጣናቸው ውጤቶች አመርቂ መሆናቸውን ጠቁመው፤ የተለያዩ ተግዳሮቶች መኖራቸውም አንስተዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ በማከል ስኬቶቻችን በጋራ ባየን ቁጥር ምን ላይ እንደደከምን፤ የቱ ጋር መተጋገዝ እንዳለብን ማየት አንዱ የዚህ መድረክ አካል ነው ያሉ ሲሆን፤ ትኩረት ሰጥተን በመወያት ለቀጣይ ስድስት ወር ትምህርት የምንወስድበት እንዲሆን በማለት መርሀግብሩን አስጀምረዋል፡፡

የግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረቡት ስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ አለሙ መንገሻ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ተግባራት በመጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ፣ በውሀ ሀብት አስተዳደር፣ በኢነርጂ ልማት እንዲሁም የክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮዎችና የተጠሪ ተቋማትን ቁልፍ ውጤት አመልካች፤ በፕሮግራም በጀት አፈጻጸም፤ በአቅም ግንባታ ዙሪያ ያጋጠሙ ችግሮች፤ የተወሰዱ መፍትሄዎች እንዲሁም በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል ፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የሚንስቴር መስሪያ ቤቱ እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች ፣ የክልል ውሀና ኢነርጂ ቢሮ አመራሮች፤ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ይሚሳተፉ ሲሆን 2ኛ ቀኑን በያዘው መርሃግብር ነገም የሚቀጥል ይሆናል፡፡

Share this Post