ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚገነባ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የኮንትራት ውል ተፈረመ፡፡

ከ49 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚገነባ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የኮንትራት ውል ተፈረመ፡፡ ግንቦት 01/2015 ዓ.ም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጋር ከ1.5 ቢልዮን ብር በላይ ወጪ የሚገነባና ከ49 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የኮንትራት ውል ተፈራረመ። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ እንደገለጹት ፕሮጀክቱ በሱማሌ ብሔራዊ ክልል ሊበን ዞን ጉራዳሞሌ ወረዳ የሚተገበር ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ ለድርቅ ተጋላጭ የሆነ አከባቢ የሚገነባ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት እንደመሆኑ በተቀመጠው የግንባታ ጊዜ ወቅቱን ጠብቆ በጥራት በልዩ ትኩረት እንደዲከናወን አሳስበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽንን በመወከል ስምምነቱን የፈረሙት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢ/ር ዮናስ አያሌው በበኩላቸው ተቋማቸው የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው በመሆኑ በገቡት ውል መሠረት ፕሮጀክቱን እንደሚያጠናቀቁ እምነታቸውን ገልጸዋል። ፕሮጀክቱ ከአለም ባንክ የአንድ ቋት የመጠጥ ውሃ፣ የሳኒቴሽን እና የሃይጅን (One WaSH) ፕሮግራም በብድር የተገኘ ሲሆን፤ ይህ የባለብዙ መንደር የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም የሚችል የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ከ49ሺ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል። የውል ስምምነቱ አጠቃላይ የሲቪል የግንባታ ስራዎችን፣ የአሌክትሮሜካኒካል ስወራዎችንና የመስመር ዝርጋታን የሚያካትት ይሆናል፡፡

Share this Post