የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከመደወላቡ ዩኒቨርሲቲና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከመደወላቡ ዩኒቨርሲቲና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ። ጥር /2015ዓ.ም (ው.ኢ .ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዋቢሸበሌ ቤዚን ፕላን የደረሰበትን ደረጃ የቴክኒክ ግምገማ፤ የቤዚን ፕላን ትግበራና የባለድርሻ አካላት ትብብርና ቅንጅታዊ አሰራር ስርዓት ዙሪያ ከመደወላቡ ዩኒቨርሲቲና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ተወያዩ። የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ በላይነህ ይርዳው ሲሆኑ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ስርዓት ለማስፈን የምንከተለው የተፋሰስ ዕቅድን በመሆኑ የዋቢሸበሌ ቤዚን ፕላን ዝግጅት በተቀመጠው ቢጋር መሠረት ሲሰራ ቆይቶ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ የተላከውን ሪፖርት (progress report) በተቋቋመው ኮሚቴ ግምገማ መካሄዱን ገልፀው ቴክኒካል ኮሚቴው ሪፖርቱን የገመገመበትን አግባብ አቅርቦ የጋራ ለማድረግ የታሰበ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል። በመድረኩ ስለ ቤዚን ፕላን ፅንሰ ሃሳብ፣ መዋቅር፣ ደንብና ሂደት የተገለፀ ሲሆን መዳወላቡ ዩኒቨርሲቲም የደረሰበትን ደረጃ ሪፖርት (Progress Report on Wabi Shebele River Basin Plan) ቴክኒካል ኮሚቴው የገመገመበት አግባብ እንዲሁም የባለድርሻ አካላት ትብብርና ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓት አስመልክቶ በቀረበው ሰነድ ዙሪያ በሰፊው ውይይት ተደርጎበታል።

Share this Post