የውሃ ሀብት አስተዳር ዘርፍ የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ውይይት ተጠናቀቀ፡

በአዳማ ሲካሄድ የቆየው የውሃ ሀብት አስተዳር ዘርፍ የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ውይይት ተጠናቀቀ፡ ጥር /2015ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ)በውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ የቀጣይ ስድስት ወራትን የስራ አቅጣጫ በማመላከት ተጠናቀቀ፡፡ በእለቱ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ ላለፉት ስድስት ወራት በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት ያሉበትን ደረጃ በመፈተሸ በተግባራት ክንውን ወቅት የነበሩ ችሮችን መለየት እዲሁም ዝቅተኛ አፈጻጻም የታየባቸው ተግባራት በመቀጣይ ስድስት ወራት ተሻሽለው የተነሳንበትን የተቀናጀና ዘላቂነቱ የተረጋገጠ የውሃ ሀብት አስተዳደር ለማስፈን ውይይቱ ወቅታዊና አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው በአመራርና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ደረጃ ያሉ የማኔጅመንት አባላት ባሉበት የጋራ ውይይት መደረጉ ችግሮችን በመለየት ባለቤት ለመስጠት ብሎም መፍትሄ ለመፈለግና በቀጣይ ለሚከናወኑ ተግባራት መደላድል ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ ነው ብለዋል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም መድረኩ ተቋማዊ መዋቅሩን ተከትሎ ሰራተኛው የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ የተጣለበትን ሀላፊነት በሚገባ ከመረዳት ረገድ ያለው ግንዛቤ ምን ያክል እንደሆነ የተረዳንበት መሆኑ እንዲሁም አዲሱ ሪፎርም ምን ይዞ እደመጣ ፣ ሰራተኛው ከተልዕኮው ጋር እንዴት እየተራመደ እንዳለ የታየበት፣ ባለድርሻዎችንና አጋር አካላትን አጋዥ አድርጎ በመውሰድ ወደ ተግባር በመቀየር ውጤት ከማምጣት አኳያ ያለውን አፈጻጸም በሚገባ ማየት የተቻለበትን እድል የፈጠረ፣ ተሳታፊዎች በቡድን በመሆን ራሳቸውን እንዲፈትሹ ጠንካራ ውይይት የተደረገበት መሆኑን አብራተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በውይይት ወቅት የተገኙ ሀሳብ አስተያየቶችንና ተሞክሮዎችን በግብዓትነት መውሰድ እንደሚገባ፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም የተግባራት አፈጻጸሙን በቅርበት እየተከታተለ እና እየተቆጣጠረ ሲመራ የቆየበትን አግባብ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ብሎም በቀጣይም የዕለት ተዕለት ስራዎችን በየሁለት ሳምንቱ በሚደረገው የሪፖርት ቅብብሎሽ እየተገመገመ የሚመራበት ስርዓት የተዘረጋ መሆኑን አክለዋል ፡፡ በቡድን ውይይቱ በርካታ ሀሳብ አስተያየቶች የተንጸባረቁ ሲሆን ከነዚህም መካከል የቀረቡ ሪፖርቶች ፣ በአሰራር ሂደት ውስጥ የነበሩ ችግሮች በግልጽ መውጣት መቻላቸው፣ እቅድ ላይ ከላይኛው አመራር አስከ ታችኛው ባለሙያ ድረስ በበቂ ሁኔታ ግንዛቤ ማስጨበጥ እንደሚገባ፣ የጋራ ግብ ላይ የተለያየ ግንዛቤ መኖር፣ አቅምን ከመገንባት አኳያ በደንብ መሰራት እንዳለበት የሚሉ ከአራቱም የቡድን ውይይት በስፋት የተንጸባረቁ ናቸው፡፡ በመጨረሻም በክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በተሰጠ የማጠቃለያ ሀሳብና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ መርሃ ግብሩ ተቋጭቷል፡፡

Share this Post