የዉሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ውይይት ተካሄደ

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዉሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ውይይት ተካሄደ። =========== ጥር 06/2015አ.ም (ውኢሚ) የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ላይ ከዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች በአዳማ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። የስድስት ወሩን እቅድ አፈጻጸም በመገምገም ማነቆዎችን መለየትና መግባባት ላይ መድረስ ብሎም በየዘርፉ ተመሳሳይ ግንዛቤ መያዝ እና የቡድን መንፈስ እንዲጠናከር ማድረግ የውይይቱ የትኩረት አቅጣጫ ሲሆን የሀይድሮሎጅ እና የተፋሰስ ዘርፍ፣ የተቀናጀ የውሃ ሀብት ዘርፍና የቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤቶች እቅድ አፈጻጸም ለውይይት ቀርቧል። በቀረቡ ሪፖርቶች መነሻነት ተሳታፊዎች በቡድን በመሆን ተቋማዊ ስትራቴጅያዊ ግቦች፣ በውጤት አመላካችና የተግባራት ትስስር፣ የአጋርና ባለድርሻ አካላት የመረጃ ልውውጥ፣ የሰራተኛ ስምሪት ፣ የአመራር ተግባራት እንዲሁም የውጤት ትስስርና አቅምን መገንባት በሚሉ የመነሻ ሀሳቦች ሰፊ ውይይት ተደረገ።

Share this Post