የገና በዓለን በማስመልከት የማዕድ ማጋራት መርሃግብር ተካሄደ፡፡

የገና በዓለን በማስመልከት የማዕድ ማጋራት መርሃግብር ተካሄደ፡፡ ታህሳስ 28/2015ዓ.ም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በተቋሙ ግቢ ውስጥ ባዘጋጀው የማዕድ ማጋራት መርሀግብር በቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 04 ለሚገኙ 100 አቅመደካሞች እና ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው 300 ሰራተኞች የተለያዩ የበዓል መዋያ ግብዓቶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡ የውሀና ኢነርጂ ሚ/ር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ያለውን ተካፍሎ አብሮ መብላት እና መጠጣት የኢትዮጵያውያን ትርጉም ያለው የቆየ ባህላችንና የአንድነታችን ምልክት መሆኑን አስታውሰው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተለያዩ ጊዜያት በዚሁ መልክ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ማዕድ ሲያጋራ እንደቆየና በዛሬው እለት ደግሞ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የተቋሙን ሰራተኞች የማእድ ማጋራቱ አካል መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ አያይዘውም እንደሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን በዓልን በዚህ መልኩ ለማክበር ሲታሰብ ሶስት ዓላማ በማንገብ ሲሆን ለቤተሰቦቻችን አጋርነትን ለማሳያት፣ ያለንን ማካፈላችን ሌሎችም አቅማቸው በፈቀደ መጠን ተካፍሎ የመብላት ባህላችንን ጠብቀው እንዲኖሩ ለማድረግ እና ለልጆቻችን መስጠትን ለማለማመድ ታሳቢ የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዕለቱ ከአጋር አካላት በተገኘ ድጋፍ 2 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገባቸው ዱቄት ለበዓል መዋያ የሚሆኑ ግብዓቶችን ድጋፍ ማድረግ ተችሏል፡፡ የደም ልገሳ መርሃ ግብርም የዝግጅቱ አንድ አካል ነበር፡፡

Share this Post