የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ተፋሰስ የተፋሰስ ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።

የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ተፋሰስ የተፋሰስ ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ። ታህሳስ 26፣ 2015 ዓ.ም.(ው.ኢ.ሚ)የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ተፋሰስ የ15 ዓመት የተፋሰስ ዕቅድ የአተገባበር ስልት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ። የውሃ ሀብቱን በፍትሀዊነት እና በዘላቂነት ለመጠቀም የውሃ ሀብት አስተዳደርን በአግባቡ በመተግበርና በመከተል በውሃ ላይ የሚስተዋሉ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ችግሮች መቅረፍ እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፤ የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አብርሀ አዱኛ በውይይት መክፈቻ ላይ አሳስበዋል። አክለውም ይህ የተፋሰስ ዕቅድ በአግባቡ ከተተገበረ ችግሮቹን ለመቅረፍ ቀላል እንደሆነም ገልጸዋል። በዕለቱም በተፋሰሱ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን መሰረት አድርጎ በዕቅዱ ውስጥ የተካተቱ አራት የትኩረት መስኮች ማለትም፤ የውሃ ሀብት አጠቃቀም እና ፍትሀዊ የውሃ ምደባ፤ በውሃ ጥራትና ብክለት ቁጥጥር፣ የሀይቆችና ረግረጋማ መሬት አስተዳደር ፤ የተፋሰስ ልማትና እንክብካቤ እና ከውሃ ጋር የተያያዘ የተፈጥሮ አደጋና የባለድርሻ አካላት ቅንጅት የአተገባበር ዕቅድ በአዘጋጆቹ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

Share this Post