በአፋር ክልል ጭፍራ ወረዳ ጉብኝት እየተደረገ ነው፡፡

በአፋር ክልል ጭፍራ  ወረዳ ጉብኝት እየተደረገ ነው፡፡ ተህሳስ 18/2015 ዓ.ም.በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር በክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራው ልዑክ በጦርነቱ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት ከደረሰባቸው ከተሞች መካከል በአፋር ክልል ጭፍራ  ወረዳ በመገኘት ጉብኝት እያደረጉ ነው ፡፡ የጭፍራ ከተማ በ3ዙር ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ውድመት የደረሰባት ሲሆን፤ በተለይ የከተማው የመጠጥ ውሀ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ በመሆኑ፤ ልዑካን ቡድኑ በመልሶ ማቋቋምና ጊዜያዊ መፍትሔ በመስጠት እየተሰራ ያለውን ስራ ተመልክተዋል ፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ በመልሶ ማቋቋም ስራ ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚንኒስቴርና የክልሉ መንግስት በቅንጅት ትኩረት በመስጠት የተሻለ ስራ እንደሚሰሩ ገልጸው፤ የሚመለከታቸው አካላትም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Share this Post