በሀገር ውስጥ አማራጭ ኢነርጂ ቴክኖሎጂ በማምረት የውጭ ምንዛሪ ማዳን ይቻላል ተባለ።
ታህሳስ 14/2015ዓ/ም በባህርዳር ከተማ የውሃና ኢነርጂ ሚኒሰቴር የሚመራ አብረምባ ቴክኖሎጂ የሃይል ቆጣቢ ማምረቻና እና የፎሴራ የሃይል ቆጣቢ ሶላር መገጣጠሚያ ከምፓኒ ዎች ጉብኝት ተደርጓል።
አብረምባ ቴክኖሎጂ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሀገር በቀል የሃይል ቆጣቢ የመኖሪያ ቤቶች የሶላር መብራት ማምረቻ ሲሆን የፎሴራ የሶላር ዕቃዎች መገጣጠሚያ የጀርመን ከምፓኒ ነው።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒሰቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለፁት ኢትዮጵያ የኃይል ቆጣቢ ቴክኖሎጂን በሀገር ውስጥ በመገጣጠም 15% የውጭ ምንዛሪ ማዳን የሚቻል ሲሆን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ማምረት ደረጃ ስትደርስ 50% የውጭ ምንዛሪ ማዳን ያስችላል ብለዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘውም በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የሆነ የሃይል ፍላጎት በመኖሩ የግል ባለሀብቱ በዘርፉ ላይ መዋለ ንዋቸውን ቢያፈሱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ብለዋል።
በጉብኝቱ ላይ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት የተሳተፉ ሲሆን SNV የተባለው የኔዘርላንድ የልማት ድርጅት; የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩቱ እና የተለያዩ የአማራ ክልል ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ተጠቃሽ ናቸው።
በመጨረሻም ድርጅቱ ከሚመለከታቸው አካላት ተገቢ ድጋፍ ቢደረግለት በእውቀት ሽግግር እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ችግሮችን በማቃለል ረገድ የተሻለ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይታመናል።