የውሃ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሚኒስቴር መ/ቤቱን ጎበኙ።

የውሃ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሚኒስቴር መ/ቤቱን ጎበኙ። ታህሳስ/2015 ዓ.ም(ው.ኢ.ሚ) የውሃ መስኖ፣ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርን ጎበኙ፡፡ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ሲያስተላልፉ፤ ተቋሙ በሪፎርም ውስጥ ማለፉን ገልጸው በበጀት ዓመቱ በርካታ ስራዎች መከናወቸውንና የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገምና ለማበረታታት በተቋሙ በመገኘታቸው አድናቆታቸውን ገልጸው ለሚደረግላቸው ድጋፍ በማመስገን በፅ/ቤት ኃላፊው የተዘጋጀውን አጠቃላይ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የተከናወኑ ተግባራትን ለም/ቤቱ እንደሚቀርብ ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም የክቡር ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሙሻ ኃይሉ ለመስክ ምልከታ በተዘጋጀው ቼክሊስት መሰረት ባቀረቡት ፅሁፍ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ነባር ተቋም ቢሆንም በ2014 በጀት አመት በአዲስ መልክ የተዋቀረ ተቋም ሲሆን የተሰጠው ስልጣንና ተግባር ለማሳካት የሚያስችል ተቋማዊ አደረጃጀቱን ገልፀው ከሰራተኛ ምደባ ጀምሮ የተሰሩ ስራዎችን ለተከበረው ምክር ቤት አባላት አቅርበዋል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው የቀረበውን ሪፖርት አዳምጠው በተቋሙ ግቢ ውስጥ የተሰሩ ስራዎችንና የህፃናት ማቆያ ማእከሉንም ተዛዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ በግቢ ውስጥ እየተሰሩ ያሉትን የለውጥ ስራዎች ከጎበኙ በኋላ ሰራተኛውን በስብሰባ አዳራሽ ባወያዩበት ጊዜ ከባለፈው ምልከታ በታዩ ጠንካራና ሊሻሻሉ በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በሰፊው ተወያይተዋል፡፡ በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ፈትያ አህመድ ከተከበረው የምክር ቤት አባላት ጋር ከሰራተኛው በተነሱ ጉዳዮች ላይ በተቋሙ አመራሮች ምላሽ የተሰጠበት ሲሆን እንደ አጠቃላይ ከዕቅድ እስከ ሪፖርት ጥሩ የግንኙነት ስርዓት ተዘርግቶ እቅድና ሪፖርትን በወቅቱ ለሚመለከተው አካል የሚደርስበት ሲስተም መዘርጋቱ፣ ከሪፎርም አንፃር ሰራተኛው ስጋት ላይ የነበረ ቢሆንም በሰራተኛ ምደባ ወቅት ግልፅነት መኖሩ፣ ከቡድን መሪ በላይ የነበረው የአመዳደብ ሂደት ሌላ ተቋም ላይ ያልታየ መሆኑን፣ ከሪፎርሙ በኋላ የቢሮ አመዳበብ በዘርፍ መሆኑና ለሰራተኛው ምቹ መሆኑን፣ ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም አንፃር ለምሳሌ IFMIS እና ISMIS እንዲሁም መረጃ መለዋወጫ KoBo toolbox ለመጠቀም የሚደረገው ጥረት፣ ከተጠሪ ተቋማት ጋር ያለው ግንኙነት፣ በተቋሙ ግቢ ውስጥ አነስተኛ ተከፋዮችን ለመደገፍ ምግቤን ከደጄ በሚል በሳር የተሸፈኑ ቦታዎችን በማልማት የጓሮ አትክልቶችን አልምተው እንዲጠቀሙ የማድረግ ስራና ግቢውን የተለያዩ ግንባታዎችን በማሰራት ምቹ ስራ ቦታ ለመፍጠር የተደረጉ ጥረቶች በጥንክሬ የታዩ መሆኑን ገልፀው በውስንነት ጉዳዮች ላይ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባ ገልፀው ውይይታቸውን አጠናቀዋል፡፡                   +6     s                      

Share this Post