ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የዋሽ ፕሮግራም፤ የቴክኒክ ድጋፍ ፕሮጀክት ትግበራ የሶስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የዋሽ ፕሮግራም፤ የቴክኒክ ድጋፍ ፕሮጀክት ትግበራ የሶስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡ ህዳር/2015 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በብዝሃ መንደር ላይ የድህረ ግንባታ የቴክኒክ ድጋፍ የፕሮጀክት ትግበራ የሶስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡ ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት ንግግር ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ እንደገለጹት ፕሮጀክቱ፤ የዋሽ ስርዓት አተገባበርን ለማጠናከር፤ የጥገናና የመለዋወጫ እቃዎች አቅርቦት ስርዓት ለመዘርጋት፤ ሀገርበቀል የሀብት ማሰባሰብን ለማሳለጥ የፋይናንስ ስትራቴጂ ለመንደፍ እና በመሳሰሉት ላይ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የፕሮጀክቱ ተወካይ አቶ ገ/እግዚአብሔር አንዷለም እንደገለጹት ፕሮጀክቱ በእንግሊዝ መንግስት ድጋፍ የሚደረግና በ9 ሚሊዮን ፓውንድ በ4 አመት የሚጠናቀቅ ሲሆን በዋናነት በድርቅ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች በ8 ክልሎች ላይ፤ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በሱማሌ፣ በቤኒሻንጉል፣ በሲዳማ፤ በትግራይ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል እንደሚተገበር ገልፀው በባለብዙ መንደር የውሃ ተቋማት ላይ በስልጠናና በሎጅስቲክ ከ30 እስከ 40 የሚሆኑ የመጠጥ ውሃ ተቋማትን የመደገፍና የማጠናከር ስራ የሚሰራ ፕሮጀክት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ስምምነቱን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጲያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ከSCRS WASH Technical Assistance project የስራ ኃላፊዎች ጋር ተፈራርመዋል፡፡

Share this Post