በስርአተፆታና አካቶ ትግበራ በህግ ማእቀፎች እና ስምምነቶች ላይ ስልጠና ተሰጠ።

በስርአተፆታና አካቶ ትግበራ በህግ ማእቀፎች እና ስምምነቶች ላይ ስልጠና ተሰጠ። 16/3/2015(ዉ.ኢ.ሚ)የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአካቶ ትግበራ፣ስርአተ ፆታ ኦዲት፣በስርአተ ፆታ ትንተና፣ በሴቶችህፃናት፣ወጣቶች ፣አረጋዉያንና አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ በወጡ የህግ ማእቀፍ እና ስምምነቶች ዙሪያ ለሚኒስቴሩ ሴት አመራ ሮች፣ አማካሪዎች፣ በሀላፊነት ላይ ላሉና ከተጠሪ ተቋማት ለመጡ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ ። ስልጠናውን በንግግር የጀመሩት የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ የዉብ ዳር አሚኖ እንደገለጹት ይህ ስልጠና ሲዘጋጅ በአመራር ላይ ያለው አካል የወጡ የህግ ማእቀፎችን በመረዳትና ሁሉም የስራ ክፍል ስርአተ ጾታን አካቶ በመተግበር ሂደት ውስጥ ስራዎችን በጋራ በመስራትና የጋራ በማድረግ ያለብንን ሀላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ያስችለናል ብለዋል። ስልጠናው በተለያዩ የስርአተ ፆታ የህግ ማእቀፎችና በሴቶች ላይ በወጡ ፓኬጆች ላይ ያተኮረ ና ሁሉም ሰራተኛ በስርአተ ጾታ ላይ ግንዛቤ በመያዝ በሚንስቴር መ/ቤታችን ለሚተገበሩ ተግባራት የሴቶችን ተሳተፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ለማሳደግ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ሰልጣኞች ስልጠናውን ከመወሰድ ባሻገር ወደ ስራ በመግባት በሚኒስትር መ/ቤታችን በተለይ ለአካል ጉዳተኞች እና ስርአተ ጾታ ላይ ከወረቀት ባለፈ ያገኙትን ግንዛቤ ወደ መሬት በማውረድ ተግበራዊ ማድረግና ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር ውጤት ማምጣት እንደሚገባቸው ተገልጿል። አገራችን ሁሉንም በሚባል ደረጃ አለም አቀፍ ስምምነቶችንና የህግ ማእቀፍች ተቀብላ የፈረመች ቢሆንም በአፈጻጸም ደረጃ ግን ገና ብዙ መስራትና ትግልን ይጠይቃል ተብሏል፡፡ ለህግ ማእቀፎች ተግባራዊነት ሁሉም ዜጋ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚጠበቅበት ተገልጿል።

Share this Post