የኢንጅነሪንግና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ለዘላቂ ልማት ለመጠቀም የኢነርጂ ድርሻ የላቀ መሆኑ ተገለጸ።

የኢንጅነሪንግና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ለዘላቂ ልማት ለመጠቀም የኢነርጂ ድርሻ የላቀ መሆኑ ተገለጸ። ሚያዚያ /2017ዓ.ም (ው.ኢ .ሚ) የኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ለዘላቂ ልማት እና ተግዳሮቶች በሚል ርዕስ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ ላይ የኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ለዘላቂ ልማት ለመጠቀም ኢነርጂ የራሱ የሆነ ሚና እንዳለው ተገልጿል። በኮንፈረንሱ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር የኢነርጅ ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ በአለም ላይ የተከሰተውን የነዳጅ ዘይት ቀውስ ተከትሎ የተለያዩ ጥናቶች እየተካሄዱ ነው ብለዋል። የአንድ ሀገር የኢነርጂ ፍጆታን ለማሳደግ እና የታዳሽ ሀይል ለመጠቀም የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል። አሁን ላይ የጀመርነውን የልማት እንቅስቃሴ እና የኢኮኖሚ እድገት በማሳካት ብልጽግናን ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው አዋጭ እና ጥራቱን የጠበቀ የኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ለዘላቂ ልማት ለመጠቀም ኢነርጂ የራሱ የሆነ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። በተለይ በታዳሽ ኢነርጂ ልማት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በቴክኖሎጂ የታገዙ፣ ብቃትና ክህሎት ያላቸው ተማሪዎችን ማፍራት ለኢነርጂና ለውሀው ዘርፍ አስፈላጊ በመሆኑ በቀጣይ ከዩንቨርስቲዎች ፣ከቲቪቲ፣በዘርፋ ከሚሠሩ ከውስጥና ከውጭ አገር ተቋማት በጋራ መስራት እንደሚገባ ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው ተናግረዋል። የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው 6ኛው የኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ለዘላቂ ልማት እና ተግዳሮቶች ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ 14 የምርምር ሥራዎች የቀረቡ ሲሆን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ኢ/ር አብደላ ከማልን ጨምሮ ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፣ ከተለያዩ የሀገር ውስጥና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት የተወጣጡ ተመራማሪዎች በአካልና በኦንላይን ተሳትፈውበታል።

Share this Post