የውሃ አገለግሎት ክፍያ ለመወሰን በተዘጋጀው ረቂቅ ደምብ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

የውሃ አገለግሎት ክፍያ ለመወሰን በተዘጋጀው ረቂቅ ደምብ ላይ ውይይት ተካሄደ ፡፡ 20/3/2015 (ው.ኢ.ሚ) የውሃ አገልግሎት ክፍያን ለመወሰን በተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡ የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ እንደገለጹት ባለፈው ዓመት የተተገበረውን ተቋማዊ ለውጥ ተከትሎ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሀገሪቱ ያሉ የውሃ ሀብቶችን ለማስተዳደር እና በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚን ለመገንባት አስቻይ ሁኔዎችን በሚፈጥር መልኩ የህግና የትግበራ ማእቀፎች በማዘጋጀት ወደ ተግባር እንቅስቃሴ መግባቱን ገልጸዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አክለው ሲገልጹ፤ ተቋሙ በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት የውሃ ሀበታችንን የመጠቀም ብቻ ሳይሆን የመጠበቅና የመንከባከብ ስራዎች በስፋት ማከናወን ስለሚጠበቅ፤ የውሃ ፈቃድ መስጠት ብቻ ሳይሆን ክፍያ ስርአት መዘርጋት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስልጣንና ኃላፊነት አንድ አካል ነው ብለዋል፡፡ የውሃ ሀብት አስተዳደር ሁሉም ውሀ ተጠቃሚዎች ውሀን የሚጠቀሙበት ፈቃድ መውሰድ ብቻ ሳይሆን የአጠቃቀም ክፍያ እንዲከፍሉ የሚጠይቅ በመሆኑ የረቂቅ ደንቡ ፋይዳ ከማስከፈል ባሻገር የውሃ ሀብታችንን ጥራትና መጠን ላይ እንድንሰራ ያደረግል፡፡ የተዘጋጀው ደንብ በዋነኛነት የውሀ ሀብትን ከምንጩ ለመጠበቅ ያለመ ሲሆን በዚህ የክፍያ ስርአት የሚካተቱት ከአንድ ሄክታር በላይ የመስኖ ተጠቃሚዎች፣ አሳ በማስገር ላይ የተሰማሩ፣ ኢንዱስሪዎች፣ የውሃ ሀይል ማመንጨት ላይ የተሰማሩ አካላት፣ የውሃ የመዝናኛ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ላይ ነው፡፡ ረቂቅ ደንቡ ላይ የግንዘቤ ፈጠራ ለማናከወን ሂልቪታስ ኢትዮጵያና ሰክሰስ ፕሮጀክት ድጋፍ እንደሚያደርጉ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

Share this Post