ክቡር ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የባግላዲሽ አምባሰደር፤ አምባሳደር ናዝሩል ኢስላም እና ኢነርጂ ልማት ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ተወያዩ፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የባግላዲሽ አምባሰደር፤ አምባሳደር ናዝሩል ኢስላም እና ኢነርጂ ልማት ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ተወያዩ፡፡
ህዳር 5/2015 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ.) ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በኢትዮጵያ የባግላዲሽ አምባሰደር፣ አምባሳደር ናዝሩል ኢስላም እና ኢነርጂ ልማት ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር የሶላር ኢነርጂ ልማት ላይ ትኩረት አድርገው ተወያይተዋል፡፡
ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በውይይታቸው ወቅት እንደገለጹት ተቋማቸው በውሃ ሀብትና ኢነርጂ ልማት ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸው በተለይ የታዳሽ ሀይል ኢነርጂ ልማት ዋነኛ የትኩረት መስክ መሆኑን አውስተዋል፡፡
በሌላ በኩል የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ በበኩላቸው እንደሀገር የታዳሽ ሀይል ከልዩ ልዩ ምንጮች፤ ማለትም ከውሃ ሀይል፣ ከንፋስ ሀይል ከሶላር ሀይል፣ ከጂኦተርምልና እንደሚገኝ፤ እንዲሁም ገሪን ሀይድሮጂን ለማረት ምቹ ሁኔታ መኖሩን ገልጸዋል፡፡
የታዎር ፓወር ኮንሰልተንሲ (Tower Power Consultancy) ተወካዮች በበኩላቸው በኢትዮጵያ ቦሶላር ኢነርጂ ልማት ላይ ለመሰማራት ያላቸውን ፍላጎት የገለጹ ሲሆን፤ እስከ 200 ሜጋ ዋት ሀይል ማመንጨት የሚችል የሶላር ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት መገንባት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡
በውይይቱ ማጠቃለያም ክቡር ሚኒስትሩ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ተቋማት የተውጣጣ ግብረሃይል በመቋቋም የቀረበው ፕሮጀክት እንደሚገመገም ገልጸዋል።