ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑ ተገለጸ።
ህዳር 04/2015 ዓ.ም.( ው.ኢ.ሚ) ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የታዳሽ ሀይል ልማት ላይ ትኩረት በማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑ ተገለጸ፡፡
በግብጽ ሻርም አልሸይክ እየተካሄደ በሚገኘው በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚመክረው የኮፕ 27 መድረክ ላይ በአለምአቀፍ የሶላር ትብብር በተዘጋጀው የሶላር ኢነርጂ ተኮር የውይይት መድረክ ላይ በበበይነ መረብ ተሳትፎ ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ ከሚመረተው 5000 ሜጋ ዋት ሀይል 98% ከታዳሽ ሃይል የሚገኝ መሆኑ ገልጸው፤ 86% የሚሆነው የታዳሽ ሀይል ከውሃ ሀይል የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመካላከል በግብርና ፣ በመሬት አጠቃቀም እና በደን ልማት ዘርፎች ላይ በትኩረት ዕየተሰራ መሆኑን፤ እንዲሁም በውሃ፣ በጤና፣ በኢነርጂ፣ በትራንስፖርት እና ከከተማ መመስፋፋት ጋር ተያይዞ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የማድርግ ሂድት ላይ ትኩረት ተደርጎበት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በንግግራቸው እንዳወሱት ኢትዮጵያ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኤሌክትሪክ ሀይል ተደራሽ ለማድግ ከተያዘው እቅድ ውስጥ 65% የኤሌክትሪክ አቅርቦት ከግሪድ እና 35% ከግሪድ ውጪ ለማሟላት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው የጸሀይ ሐይል አንዱ አማራጭ መሆኑን አውስተዋል፤ ከዚህም ጋር ተያይዞ በመተሃራ ባለ100MW የጸሀይ ሀይል ፕሮጀክት፤ እንዲሁም እያንዳንዳቸው ባለ125MW የሶላር ሀይል ፕሮጀክቶች በአፋር ክልል በዲቼቶ እና በሶማሌ ክልል ጋድ በተባለ ቦታ መተግበሩን፤ እንዲሁም ትግራይ ክልል ባለ500MW የሶላር ፓርክ መገንባቱን ገልጸዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በጸሀይ ሀይል የሚሰሩ ፓምፖች የመስኖ ግብርና ስራ ላይ ማስፋፋት የምግብ ዋስትና ለማረጋጥ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ አክለው ገለጸዋል፡፡
በመጨሻም ከአለም አቀፉ የሶላር አሊያንስ ተቋም ጋር በአቅም ግንባታና ሌሎች ፕሮግራሞች ጋር በተያያዘ የሚታየውን አጋርነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡