በሁለት ዙር የተካሄደው የመካከለኛ አመራሮች ስልጠና ተጠናቀቀ።

በሁለት ዙር የተካሄደው የመካከለኛ አመራሮች ስልጠና ተጠናቀቀ። ጥቅምት 27/2015 ዓ.ም(ዉ.ኢ.ሚ)፤ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሁለት ዙር ለሥራ አስፈፃሚዎች; ለዴስክ ኃላፊዎችና ለቡድን መሪዎች በሁለት ዙር ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ። የሁለተኛው ዙር ስልጠናን አስመልክው አስተያየት የሰጡት የሚኒስቴር መ/ቤቱ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኦልቃባ ባሼ ስልጠናው በየደረጃ ያለው አመራር የተሠጠውን ሃላፊነት እና ተግባራትንበሚገባ በመረዳት ለተቋሙ ውጤታማነት የድርሻቸውን እንዲወጡ ያደርጋል ብለዋል። በሌላ በኩል በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ከፍተኛ አማካሪ አቶ አስማማው ቁሜ እንደገለጹት ስልጠናው በእቅድ አዘጋጃጀት ላይ ያለንን የግንዛቤና የእውቀት ክፍተቶችን መሸፈን የሚያችል ነው ብለዋል። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ በላይነህ ይርዳው በበኩላቸው፤ ስልጠናው ቁልፍ የአፈፃፀም አመልካች (Key performance indicator) ላይ ያለንን ግንዛቤ በማሳደግ የፕሮግራም በጀት ዝግጅት እና የእቅድ ትግበራ ላይ ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚያደረግ ጠቁመዋል። በመጨረሻም በየደረጃ ያሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች ከስልጠና ያገኙትን የአመራር እና የክህሎት አቅም ግንባታን በመጠቀም ከዕቅድ ሥራ ክፍል ጋር በመቀናጀት የመደበኛና የፕሮጀክት ሥራዎች እንዲያሰልጡ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል::

Share this Post