የአለም ውሃ ቀን "ውሃን ለሰላም" በሚል መሪ ቃል ተከበረ።

የአለም ውሃ ቀን ውሃን ለሰላም በሚል መሪ ቃል ተከበረ።

መጋቢት 13/2016 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የአለም ውሃ ቀን ውሃን ለሰላም በሚል መሪ ቃል በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ በተለያዩ ዝግጂቶች ተከበረ፡፡

በዓሉን በንግግር የከፈቱት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የክቡር ሚኒስትር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ማሙሻ ሀይሉ ውሃ ሂወት ነው ስንል ሂወት ላለው ነገር በሙሉ መሰረት መሆኑን እንደሚያሳይና ውሀን ለሰላም ስንል ደግሞ ዘርፈ ብዙ ለሆኑ ጉዳዮች እንደሚያገለግልና ጥቅም ላይ በምናውልበት ጊዜ በፍትሀዊነትና በስምምነት ለሁሉም በሚበቃ መልኩ መጠቀም የምችልበትን ምቹ ሁኔታ ስለሚፈጥር ነው ብለዋል።

እንደ ሀላፊው ገለጻ የእለቱ ውይይት በሶስት ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ሴቶች በውሃ የመጠቀም ትልቅ ድርሻ ስላላቸውና ለሰላም ያለቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በውሃ ዲፕሎማሲው ላይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ እዲሆኑ ታሳቢ ያረገ ውይይት ነው ብለዋል፡፡

አክለውም ውሃን ለመጠቀም ሲታሰብ ለምን አይነት፣ የት ቦታ፣ እንዴት እና ማን ነው የሚጠቀመው የሚሉ መረጃዎችን በማደራጀት በአግባቡ በመያዝ ስለ ውሃ ያለንን ግንዛቤ አስፍተን ማወቅ እንዳለብን በማሳሰብ መርሀ ግብሩን አስጀምረዋል፡፡

የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ዶ/ር ሚካኤል በበኩላቸው በሀገራችን ድንበር ተሻጋሪ የውሀ ሀብቶች በመኖራቸው ከአጎራባች ሀገራት ጋር እዴት በሰላም መጠቀም አለብን፤ እንዴትስ ፍትሀዊ የሆነ የውሀ ክፍፍል ማምጣት ይቻላል፤ በሚሉና በመሳሰሉት እርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ ባደረጉበት ወቅት በዚህ አመት "ውሃ ለሰላም" በሚል መሪ ቃል መከበሩ የውሃ አጠቃቀም ሊያስከትል የሚችለውን ችግር ለመቅረፍ፤ በውሃ አጠቃቀም ዙሪያ የወንዶችና ሴቶችን እኩልነት ለማጎልበት፣ ድህነትን ለመቀነስ፣ ሰላምና ደህንነትን ለማስፈን፣ የውሃ አጠቃቀመም ትኩረት እንዲሰጥበት ያደርጋል ብለዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ በተለያዩ ሙሁራንና ባለሙያዎች ጥናታዊ ጽሁፎች ያቀረቡ ሲሆን የፓናል ውይይቱም የፕሮግራሙ አንዱ አካል ነበር፡፡

በበአሉ ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች፣ አምባሳደሮች፣ አጋር ድርጅቶችና የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈውበታል፡፡

Share this Post