በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና በአማራጭ ኢነርጂ ላይ በተሰማሩ መንግስተዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር ወጥነት ያለው ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓት መተግበር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና በአማራጭ ኢነርጂ ላይ በተሰማሩ መንግስተዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር ወጥነት ያለው ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓት መተግበር እንደሚገባ ተገለጸ ፡፡

ጥር 30/2016 (ዉ.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በመላ ሀገሪቱ የመጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና አማራጭ ኢነርጂ ላይ የተሰማሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመከረበት ወቅት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት ለመስራት የአሰራር ስርዓትና አደረጃጀት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑ ተነግሯል፡፡

መርሀግብሩን በንግግር የከፈቱት የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ መርሃግብሩ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና የኢነርጂ ልማት ላይ የተሰማሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር ሲነርጂ በመፍጠር ላይ፤ ሀብት በማሰባሰብ እና በመጠቀም ሂደት ላይ፣ እና ወጥ የሆነ የግንኙነት እና የአሰራር ስርዓት ከመፍጠር አንጻር መድረኩ ያለውን ፋይዳ በማንሳት መድረኩን አስጀምረዋል፡፡

መርሀ ግብሩ ላይ የክቡር ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አቶ አበራ እንዳሻው የዳሰሳ ጥናት ባቀረቡበት ወቅት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በውሀና ኢነርጂ መስክ ለሚሰሩ ድርጅቶች የህግ ማእቀፎችን በማውጣት የመደገፍ የመከታተልና የማስፈጸም ስራን ይሰራል ብለዋል። በዚህም መስሪያ ቤቱ ከክልሎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ፕሮግራሞችን አቅዶ እየሰራ ይገኛል ያሉት አማካሪው ለነዚህ ስራዎች በቀጥታ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የሚመለከት ስራ ክፍል ለማቋቋም ሀገር አቀፍ ፈጣን የዳሰሳ ጥናት በ5 ክልሎች እየተንቀሳቀሱ ያሉ14 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ላይ መሰራቱን ገልጸው፤ በነዚህ ክልሎች ውጤታማና ጥሩ አሰራር ያለቸው ድርጅቶች እንዳሉ ሁሉ ክፍተቶች ያለባቸው ድርጅቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡

የዳሰሳ ጥናቱ ላይ ለተነሱ ሀሳብ አስተያቶች ክቡር ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ እና አቶ ፋሲካው ሞላ የሲቪል ማህረሰብ ድርጂቶች ምክትል ዋና ዳይሬክተር ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ፋሲካው ሞላ የሲቪል ማህረሰብ ድርጂቶች ምክትል ዋና ዳይሬክተር የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጠንክሮ ወደታች በመውረድ ስራዎችን እየገመገመ በመሄድ ውጤቱን ማየት አለበት በማለት ባለስልጣኑም ከጎኑ በመሆን ድጋፍ እንደሚያደርግ በመግለጽ ሌሎች መስሪያ ቤቶች ከዚህ ትምህርት መውሰድ አለባቸው በማለት አሳስበዋል፡፡

መውይይቱ ላይ የክልል ውሀ ቢሮ ሀላፊዎች፣ ከ100 ባላይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጂቶችና የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈውበታል፡፡

Share this Post