በክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ የተመራ ቡድን በህንድ ኢነርጂ ሳምንት እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

በክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ የተመራ ቡድን በህንድ ኢነርጂ ሳምንት እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

የካቲት 01/2016 ዓ.ም. ( ው.ኢ.ሚ) በኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ የተመራ ቡድን እ.ኤ.አ ከየካቲት 6 እስከ የካቲት 9/ 2024 በህንድ እየተካሄደ በሚገኘው የሕንድ የኢነርጂ ሳምንት እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

ክቡር ሚኒስተር ዴኤታው አሁናዊ እና የመጪው ጊዜ የሀይል ፍላጎት ልየታና ትንበያ፤ እንዲሁም የሀይል አቅርቦት እጥረት ተጋላጭነት ላይ ትኩረት ባደረገው የዘርፉ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ በመገኘት በተለይ በኢትዮጵያ የታዳሽ ሀይል ሀብት አቅም ላይ፤ የታዳሽ ሀይል የማመንጨት ስራዎችንና ተግዳሮቶችን በተመለከተ እና በታዳሽ ሀይል ልማት የኢንቨስትመንት እድሎች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የዘርፉ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ከኔዘርላንድስ መንገስት የኢነርጂ ዘርፍ ልዩ መልእክተኛ Mr Frederik Wisselink ጋር የባዮጋዝ ስራዎችን በማስፋፋት ዙሪያ ላይ፤ እንዲሁም ከህንድ የፔትሮሊየም እና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ሚኒስትር Shri Hardeep Singh Puri ጋር በኢነርጂ ልማት ውይይት አድርገዋል፡፡

Share this Post