ነፃ፣ ገለልተኛ እና አካታች የሆነ ጠንካራ ሲቪል ሰርቪስ ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ተገለፀ።

ነፃ፣ ገለልተኛ እና አካታች የሆነ ጠንካራ ሲቪል ሰርቪስ ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ተገለፀ።

ጥር 30 /2016 ዓ/ም ነፃ፣ ገለልተኛ እና አካታች የሆነ ጠንካራ ሲቪል ሰርቪስ ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ተገለፀ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች እና ስራተኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተደረገ የሚገኘው ስልጠና በሁለተኛ ቀን ውሎው በኢትዮጵያ አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት የተደረገ ታሪካዊ ዳራ ላይ በክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ ገለጻ ተደርጓል።

ክቡር አማካሪው አያይዘውም ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ ከባለፉት መንግስታት ጀምሮ ተግዳሮት ሆኖ የቆየ መሆኑን ጠቅሰው ፤ የዚህ መንሴ ብቃት ያለው የሰው ኃይል ምደባ ነፃና ገለልተኛ እንዳልነበር በምሳሌነት አስረድተዋል።

በዚህ ወቅትም ቢሆን ከነዚህ ዓይነት ችግሮች መላቀቅ አለመቻሉን ገልፀው፤ በአሰራርና በቴክኖሎጂ የታገዘ ነፃ፣ ገለልተኛ እና አካታች የሆነ ጠንካራ የሲቪል ሰርቪስ ስርዓት መዘርጋት ይጠበቅብናል ብለዋል ።

Share this Post