የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የስድስት ወር ስራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።

የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የስድስት ወር ስራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።

ጥር 27/2016 (ው.ኢ.ሚ) ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሰራተኞቹ ጋር የስድስት ወር ስራ አፈጻጸም ሪፓርት ላይ ግምገማ አካሂዷል

መርሀ ግብሩን የከፈቱት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሙሻ ሀይሉ ከዛሬ ስድስት ወር በፊት በእቅድ ይዘን ያጸደቅናቸውን ተግባራት ምን ላይ እንደደረሱ የሚገመገምበት መሆኑን ገልጸው፤ በተለይ በቁልፍ ውጤት አመልካች (kpi) መሠረት ምን ሰርተናል? ያጋጠሙንስ ተግዳሮቶች እንዴትስ ፈታናቸው? የሚለውን የምናይበት እና የምንገመግምበት በመሆኑ ሁሉም ሰራተኛ በትኩረት እንዲከታተል አሳስባለሁ በማለት መርሀ ግብሩን አስጀምረዋል፡፡

የ2016 ዓ.ም ግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረቡት የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ አለሙ መንገሻ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ተግባሮች በውሀ ሀብት አስተዳደር፤ በኢነርጂ ልማት እንዲሁም በመጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ዘርፎችና የተጠሪ ተቋማትን ቁልፍ ውጤት አመልካች፤ በፕሮግራም በጀት አፈጻጸም፤ በአቅም ግንባታ ዙሪያ፤ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎች፤ እንዲሁም በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል ፡፡

በቀረቡት ሀሳቦች ላይ ሰራተኞችም አስተያየት ያቀረቡ ሲሆን፤ መርሀ ግብሩ በቀጣይ ቀናት ከከልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮዎች እና ከድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ጋር እንደሚቀጥል ተጠቁሟል፡፡

Share this Post