በሩብ አመቱ ንፁህ የመጠጥ ውሃን ተደራሽ በማድረግ ውጤታማ ስራ መሰራቱ ተገለፀ።

በሩብ አመቱ ንፁህ የመጠጥ ውሃን ተደራሽ በማድረግ ውጤታማ ስራ መሰራቱ ተገለፀ። ህዳር/2016 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሩብ አመቱ ንፁህ የመጠጥ ውሃን ለዜጎች ተደራሽ በማድረግ ውጤታማ ስራ መሰራቱ ተገለፀ። ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ከሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ በ2016 በጀት አመት በመጀመሪያው ሩብ አመት አፈፃፀም ላይ ንፁህ የመጠጥ ውሃን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ በሚከናወኑ ተግባራት ጥሩ አፈፃፀም እንዳለ ገልፀው በቀጣይም ቴክኖሎጂዎችን በማላመድ እንዲሁም "ግድቤን በደጄ" መርህን ተግባራዊ በማድረግ የዝናብ ውሃን በመያዝ የውሃ እጥረት በሚያጋጥማቸው ቦታዎች ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል። በውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ተፋሰሶችን በመለየትና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም መረጃ የመሰብሰብ ተግባር እንደሚከናወን ጠቅሰዋል። ክቡር ሚኒስትሩ አያይዘውም የኤሌክትሪክ ኃይል ባልደረሰባቸው አካባቢዎች ኤሌክትሪክን ከዋናው መስመር በመሳብ ዜጎችን የኃይል ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለና ከዋናው የሀይል መስመር ውጪ ከፀሀይ ብርሃንና ሌሎች የሀይል አማራጮችን በመጠቀም በርካታ የገጠር ከተሞችን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። አክለውም በሩብ አመቱ የኦሞ ጊቤ፣ ዋቢ ሸበሌ፣ ገናሌ ዳዋና ባሮ አኮቦ ተፋሰሶች መሪ እቅድ መዘጋጀቱን ገልፀው በቀጣይ በሌሎች ተፋሰሶች መሪ እቅዱ ይዘጋጃል ብለዋል።

Share this Post