ውሃውም ኢነርጅውም የሁላችን ጉዳይ ስለሆነ አስተዋጿችን በምን መልኩ መሆን እንዳለበት የቤት ስራ የሰጠ አውደ ርዕይ።

ውሃውም ኢነርጅውም የሁላችን ጉዳይ ስለሆነ አስተዋጿችን በምን መልኩ መሆን እንዳለበት የቤት ስራ የሰጠ አውደ ርዕይ። አርቲስት ሚካኤል ታምሬ የፊልምና የማስታወቂያ ባለሙያ ታዋቂውና ተወዳጁ አርቲስት ሚካኤል ታምሬ አገር አቀፍ የውሃና ኢነርጂ አውደርእይን ከጎበኘ በኋላ ጠቃሚ ሀሳብ አስተያየቶችን ሰጥቶናል። ሀገራችን ካላት እምቅ ሀብት አንዱና ዋነኛው ውሃ ነው የሚለው አርቲስቱ ይህን ሀብት እንዴት እየተጠቀምን እንዳለ፣ወደፊት እንዴት ለመጠቀም እንደታሰበ እስካሁን የተሰሩትንና ሊሰሩ የታሰቡትን ጭምር ማየት በመቻሌ ወደፊት ትልቅ ስራ እንደሚጠበቅብን አስገንዝቦኛል ብሏል። አሁን ካለው እንዲሁም ወደፊት ከሚመጣው የህዝብ ብዛትና የኑሮ ደረጃ አኳያ አሁን ላይ እየሰራንበት ባለው ፍጥነት ሰርተን ለውጥ ማምጣት እንደማንችልም የተገነዘብኩበት አውደርዕይ ሲል ገልጾታል ። ውሃውም ኢነርጂውም የሁላችን ጉዳይ ነው የሚለው አርቲስቱ በምን መልኩ አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለብንና የድርሻችን እንድንወጣ የቤት ስራ የሰጠኝ አውደ ርዕይ ብሎታል። አከል አድርጎም ባለሙያ ላለልሆኑ ሰዎች ስለተግባራቶቹ በቀላሉ እንዲረዱ የቀረበበት መንገድም በጣም ጥሩ እንደሆነ እንዲሁም ስለተደረገለት ገለጻና ማብራሪያም ምስጋናውን አቅርቧል። የዚህ አይነቱ አውደ ርዕይ በተለያየ መንገድና አቀራረብ ቢቀጥል ተቋማት ምን እየሠሩ ነው የሚለውን ከመገመት ባለፈ አውቀነው ህዝብ የሚዳኝበትን መንገድ ስለሚፈጥር የተሰራው ስራ በጣም ጥሩ ነው ሲል ባየው ነገር መደሰቱን አርቲስቱ ነግሮናል።

Share this Post