የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አባላት አገር አቀፍ የውሃና ኢነርጂ አውደርእይን ጎበኙ።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አባላት አገር አቀፍ የውሃና ኢነርጂ አውደርእይን ጎበኙ። የኢንተርፕራይዙ ም/ስራ አስፈጻሚ እንዳሉት እንደተቋም እናገኛለን ብለን አቅደን ከመጣነው በላይ እንደ ሀገር እየተሰሩ ያሉ በርካታ ለእድገት ወሳኝ የሆኑ ነገሮችን አግኝተናል ብለዋል። ውሃ ከመነሻው እስከተገልጋዩ ለመድረስ የሚያልፍበትን ረጅም ሂደት እና እስከ ሀይል ማመንጨት ያለውን የረቀቀ የቴክኖሎጅ ጉዞ እንዲሁም ተግዳሮቶቹንና እነሱን ለመፍታት የተኬደበት ርቀት እንደተቋምም እንደ ሀገርም እየደረስንበትን ያለውን የእድገት ጎዳና የሚያሳይ መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል። እንደ ሀገር ያለን እምቅ ሀብት ብዙ ነው የሚሉት ም/ስራ አስፈጻሚው ይህንን ሀብት ወደ መሬት አውርደን መጠቀም እንድንችል አውደርዕዩ ቁጭት የሚፈጥር ነው ብለውታል። ይህ አውደ ርዕይ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሌሎች አካባቢዎች ለእይታ መቅረብ የሚችልበት ሁኔታ ቢፈጠር ሲሉም አስተያየታቸውን አክለዋል።

Share this Post