የኦፍግሪድ፣ ባክ አፕና ሀይብሪድ አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እያደረገ የሚገኝ ድርጅት።

ጳጉሜ 5 የትውልድ ቀን - ኢትዮጵያ የትውልዶች ምድር የኦፍግሪድ፣ ባክ አፕና ሀይብሪድ አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እያደረገ የሚገኝ ድርጅት። ---------------------- በአገር አቀፍ የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሽን ስራቸውን እያስጎበኙ ከሚገኙ ድርጅቶች መካከል የጎርጅየስ ሶላር ሶሊሽን ካምፖኒ አንዱ ነው። የካምፖኒው የኤሌክትሪክ ቴክኒሽያን አቶ የወንድወሰን እንዳለ እንደሚያስረዱት ካምፓኒው ሶስት አይነት አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሲሆን ከዋናው የኤሌክትሪክ መስመር ውጭ ለሆኑ ገጠራማ አካባቢዎች የሶላር አማራጮችን በማቅረብ ማህበረሰቡ በተለይም ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም ገዳማት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ይገልጻል። ሁለተኛው ቴክኖሎጅ ደግሞ በኤሌክትሪክ መብራት የሚሰራ ሆኖ ሀይልን በመቆጠብ በቤት ውስጥ የሚፈጠርን የመብራት መቆራረጥ በመተካት እንደ ተጠቃሚው ፍላጎት በስታንዳርዱ መሰረት ከ6 ሰዓት ጀምሮ እስከ 24 ሰዓት ያልተቋረጠ የመብራት አገልግሎት የሚሰጥ ቴክኖሎጂ ነው ብለዋል። በተጨማሪም ቴክኖሎጅው የሀይል መጨመርና መቀነስን በማመጣጠን በኤሌክትሪክ እቃዎች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት የሚቀርፍ ነውም ተብሏል። ሶስተኛው ደግሞ የሀይብሪድ ቴክኖሎጅ ኤሌክትሪክ እና ሶላር ሲስተምን የሚጠቀም እጅግ ዘመናዊ ሲሆን ከግለሰብ ጀምሮ እስከ ድርጅቶች በርካታ የቴክኖሎጅው ተጠቃሚዎች እንዳሉ ተናግረዋል። ድርጅቱ ስራውን ከጀመረ ሁለት አመታትን እንዳስቆጠረ የሚናገሩት ቴክኒሽያኑ ለአገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉት ባትሪዎች ጥራት ያላቸው ሲልድ የሆኑና በገጠር ለ5 ዓመታት በከተማ ደግሞ ለ10 ዓመታት አገልግሎት ይሰጣሉ ብለዋል። ካምፖኒው ቴክኖሎጅዎችን በስፋት በገጠርም በከተማም ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ጅርጅቶች እያቀረቡ እንደሆነና በርካታ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች እንዳሉአቸው ቴክኒሽያኑ ገልጸዋል፡፡

Share this Post