ከግሪድ ውጭ በርቀት የሚገኙ አካባቢዎችን ተደራሽ ለማድረግ ሚኒ ግሪዶችን ትግበራ በግሉ ዘርፍ ተሳትፎ እየተሰራ ነው ተባለ።

ከግሪድ ውጭ በርቀት የሚገኙ አካባቢዎችን ተደራሽ ለማድረግ ሚኒ ግሪዶችን ትግበራ በግሉ ዘርፍ ተሳትፎ እየተሰራ ነው ተባለ። ጷግሜ/2015ዓ ዓ.ም ከግሪድ ውጭ በርቀት የሚገኙ አካባቢዎችን ተደራሽ ለማድረግ ሚኒ ግሪዶችን በመተግበር ለማህበራዊና ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት፤ እንዲሁም ለቤተሰብ ፍላጐት በግሉ ዘርፍ ተሳትፎ እየተሰራ ነው ተባለ። በዓለም ባንክ በአፍሪካ ሚኒ ግሪድ ኘሮግራምና በGEAPP አስተባባሪነት በተዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ሱልጣን ወሊ ባደረጉት ገለጻ፤ አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ባለመሆኑ የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ኘሮግራም በመንደር ከግሪድና ከግሪድ ውጭ ባሉ ቴክኖሎዎች ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፤ በተለይ ከግሪድ ውጭ በርቀት የሚገኙ አካባቢዎችን ተደራሽ ለማድረግ ሚኒ ግሪዶችን በመተግበር ለማህበራዊና ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት፤ እንዲሁም ለቤተሰብ ፍላጐት በግሉ ዘርፍ ተሳትፎ በብዛት እየተሰራ ነው ብለዋል። ለዚህም በርካታ የልማት አጋሮች እንደዓለም ባንክ GEAPP፣ አፍሪካ ልማት ባንክ እና የጀርመን የልማት ድርጅት የመሳሰሉት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረጉ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

Share this Post