አውደርእዩ በከተማችን የሚታየውን የውሀ ችግር ለመፍታት እየተደረገ ያለውን ጥረት ያየንበት ነው፡፡

አውደርእዩ በከተማችን የሚታየውን የውሀ ችግር ለመፍታት እየተደረገ ያለውን ጥረት ያየንበት ነው፡፡ ጳጉሜ /2015 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ)በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች እና የምክር ቤት አባላት በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋውን የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ አውደርእይ ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸው ወቅትም የክፍለ ከተማው የምክር ቤት ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ በቀለ ጉታ አውደርእዩ ሀገራችን በእድገት ጎዳና ላይ መሆኗን መመስከር የሚያስችል መሆኑን ገልጸው፤ በተለይ ከከተሞች መጠጥ ውሀ እና ፍሳሽ አንጻር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት አበረታች ናቸዎ ብለዋል፡፡ በተያያዘም የውሀና ኢነርጅ ሚኒስቴር በበላይነት እየመራ የንጹህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት እና ተደራሽነት ላይ ከተማውን ከዚህ በላይ እንደሚደግፍ የወደፊት እቅዶችን ያየንበት አግባብ ተስፋ ሰጪ ነው ያሉት አፈጉባኤው፤ በአጠቃላይ የምክር ቤት አባላት ከውሀ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሚጠበቅበትን እደሚወጣ ማረጋገጥ እፈልጋለሁ በማለት ገልጸዋል፡፡

Share this Post