የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በዳውሮ ዞን በድርቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወጎኖች ሰብዓዊ ድጋፍ አደረገ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በዳውሮ ዞን በድርቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወጎኖች ሰብዓዊ ድጋፍ አደረገ፡፡ ሰብዓዊ ድጋፉን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በተርጫ ከተማ ተገኝተው አስረክበዋል፡፡ በርክክቡ ወቅት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ ስለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡ ክቡር ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በበኩላቸው ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከሌሎች ሥራ ኃላፊዎች ጋር የመጡት በክልሉ በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ ለማየት፣ በችግሮቻቸውም ዙርያ ለመወያየትና የጋራ መፍትሔ ለመፈለግ እንዲሁም በዳውሮ ዞን በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማበርከት መሆኑን ገልጸዋ፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያደረገው ድጋፍ 593 ኩንታል የበቆሎ ዱቄትና 550 ሊትር ዘይት እንደሆነ በርክክቡ ወቅት ተገልጿል፡፡

Share this Post