በአካባቢ የሚገኙ የኢነርጂ ምንጮችን በመጠቀም ከዋና መስመር የሚርቁ ቦታዎችን የሀይል ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

በአካባቢ የሚገኙ የኢነርጂ ምንጮችን በመጠቀም ከዋና መስመር የሚርቁ ቦታዎችን የሀይል ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ ግንቦት 23/2015 ዓ.ም.(ው.ኢ.ሚ) በአካባቢ የሚገኙ የኢነርጂ ምንጮችን በመጠቀም ከዋና መስመር የሚርቁ ቦታዎችን አነስተኛ የውሃ ሀይል ግድብ በመገንባት የሀይል ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ በሃድያ ዞን በጊቤ ወረዳ በሌመር ወንዝ ላይ የተገነባው አነስተኛ የውሃ ሀይል ማመንጫ በጎበኙበት ወቅት የውሃ ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ እንደገለጹት ከዋናው የሃይል መስመር የሚርቁ አካባቢዎችን የሃይል ተጠቃሚ ለማድረግ በየአካባቢው ያሉ አማራጭ የሃይል ምንጮችን መጠቀም እንደሚገባ ገልጸው፤ በጊቤ ወረዳ ሌመር ወንዝ ላይ የተገነባው አነስተኛ የውሃ ማመንጫ ግድብ የመስመር ዝርጋታው ሲጠናቀቅ በሁለት ኪ.ሜ. ክልል ውስጥ የሚገኙ ከ300 በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው መሰል የአነስተኛ የሀይል ማመንጫ ግንባታ የመሬት አቀማመጡ ሀይል ለማመንጨት ምቹ በሆኑ አካባቢዎች እንደሚቀጥልና በቀጣይ በአማራ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ ክልሎች ሶሰት የአነስተኛ ሀይል ማመንጫዎች እንደሚገነቡ ገልጸዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም የውጭ ምንዛሬ የሚጠይቁ ግብዓችን በሀገር ውስጥ ማምረት የሚቻልበትን አማራጮች ማየት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ የሃድያ ዞን ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ መምሪያ ሃላፊ አቶ መለሰ ሀይሌ እንዳሉት አነስተኛ የሃይል ማመንጫው እንደሞዴል የሚወሰድ መሆኑን ገልጸው፤ የመስመር ዝርጋታው ሲጠናቀቅ በተለይ ለሴቶችና ለተማሪዎች ከፍ ያለ ፋይዳ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡ የጊቤ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ቤታ ሌሊሶ በበኩላቸው የመስመር ዝርጋታው በአፋጣኝ ተጠናቆ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድግ መሰራት እንዳለበት ገልጸው፤ የአካባቢው ማህበረሰብ የአነስተኛ ሐይል ማመንጫ ግንባታ ላይ ድጋፍ ሲያደረግ መቆየቱንና በቀጣይም በመከለልና የተጠናከረ ጥበቃ በማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡ እስከ 25 ኪሎ ዋት የሚያመነጨው አነስተኛ የውሃ ሀይል ግድብ የመስመር ዝርጋታ በሁለት ወራት ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

Share this Post