የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመከላከል የተጠናከረ የቅድመ ማስጠንቃቂያ ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመከላከል የተጠናከረ የቅድመ ማስጠንቃቂያ ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ ግንቦት 15/2015 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ)በአየር ንብረት ለውጥ አማካኝነት የሚከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመከላከል የተጠናከረ የቅድመ ማስጠንቃቂያ ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ በጀኔቫ ስዊዘርላንድ እየተካሄደ በሚገኘው አስራዘጠነኛው የአለም ሜቲሮዎሎጂ ድርጅት ኮንግረስ እየተሳተፉ የሚገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ እንደገለጹት የአየር ንብረት ለውጥ ድርቅ፣ የጎርፍ አደጋ፣ የደን ቃጠሎና የመሬት መንሸራተት የመሳሰሉ ተፈጥሯዊ አደጋዎች መንስዔ በመሆን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ ፈተና መደቀኑን አውስተው፤ እንደማሳያ በኢትዮጵያ በደቡብና በደቡብ ምስራቃዊ አካባቢዎችና በአጎራባች ሀገራት ለተከታታይ አምስት አመታት የተከሰተው ድረቅ በሰዎች ላይና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ጠቅሰዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አክለውም በአየር ንብረት መዛባትና ለውጥ ምክንያት የሚመጡ ችግሮችን ለመቋቋም መወሰድ ከሚገባቸው እርምጃዎች መካከል አንዱ የተጠናከረ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት በመዘርጋት መረጃ ቀድሞ እንዲደርስ ማድርግ መሆኑን አውስተው፤ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት የተጠናከረ የሃይድሮ-ሜትሮሎጂ መከታተያና መቆጣጠሪያና መሠረተልማት እና የዘርፉ ተዋናዮችን ቅንጅት እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡ ክቡር ሚኒስተር ዴኤታው መልእክታቸውን ሲያጠናቅቁ እንደገለጹት መሰል አደጋዎችን ለመከላከል የቅድመ ጥንቃቄ ስርዓት ከመዘርጋት ባሻገር ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ አንስተው፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግበር በምሳሌነት መወሰድ እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡ ከግንቦት 22 አስከ ሰኔ 2/2023 በሚቆየው መድረክ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታውን ጨምሮ፤ የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢነስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ እና ሌሎች መካከለኛ አመራረሮ ተሳታፊ ናቸው፡፡

Share this Post