በአፋር ብሔራዊ ክልል በታችኛው አዋሽ ወንዝ ላይ የተጀመረው የወንዝ አመራር ስራ ተጎበኘ።

በአፋር ብሔራዊ ክልል በታችኛው አዋሽ ወንዝ ላይ የተጀመረው የወንዝ አመራር ስራ ተጎበኘ። ግንቦት 10/2015አ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ በክቡር ዶ/ር አብርሀ አዱኛ የሚመራ የከፍተኛ አመራሮችና የባለሙያዎች ቡድን በአፋር ብሄራዊ ክልልል በታችኛው በአዋሽ 3 ወረዳዎች በ123 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የተጀመረውን የወንዝ አመራር ስራ ጎብኝተዋል። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ እንደገለጹት የጎርፍ አደጋን ለመቀነስ ከተመረጡ ተፋሰሶች ዋናውና ሰፊ የሆነው የአዋሽ ወንዝ የተለያዩ ክልሎችንና ከተሞችን ስለሚነካ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍ ያለ ነው ብለዋል። ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በማከል ወንዙ በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት እያስከተለ የቆየ መሆኑን ጠቅሰው በአሁኑ ሰአት በመካከለኛው አዋሽ 3 ወረዳዎች ማለትም ገዋኔ፣ ዱለቻ እና ገልአሎ ከ123 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የወንዝ አመራር ስራ በማከናወን ችግሩን ለመከላከል እየተሰራ መሆኑንና በዚህ ፕሮግራም ተደራሽ ባልሆኑ ሌሎች ወረዳዎች ደግሞ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው እንዳሉት የወንዝ አመራር ስራው የተቋሙን በመሀንዲሶች በመጠቀም በማሽን ኪራይ ብቻ እንዲሰራ መደረጉ ወጪ መቀነስ መቻሉን ገልጸው፤ የወንዝ ዳቻዎችን የማስፋትና ከፍታቸውን የመጨመር ስራ ተጠናቆ ለሚፈለገው አገልግሎት እንዲውል ተጨማሪ ማሽኖችን በማስገባት ተጨማሪ ሰዓት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አብዲ አሊ እንዳሉትም የአዋሽ ወንዝ በየአመቱ በአካባቢው የሚኖሩ ማህበረሰቦችን በማፈናቀልና ንብረት ላይም ጉዳት ሲያደርስ እንደነበር ጠቅሰው አሁን እየተሰራ ያለው የወንዝ አመራር ስራ የወንዙን ፍሰት በማስተካከል፤ የሚደርሰውን የጎርፍ አደጋ ይቀንሳል ብለዋል። የአካባቢው ነዋሪዎችም እንደለጹት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በየካቲት ወር መጥተው ችግሩን መመልከታቸውን አውስተው መፍትሄ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አመስግነው ስራው በሌሎች ወረዳዎችም ወረዳዎችም ተግባራዊ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡

Share this Post