በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር በክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራ ቡድን ጂንካ ገባ።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር በክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራ ቡድን ጂንካ ገባ። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራ የአመራሮችና የባለሙያዎች ቡድን በደቡብ ኦሞ ዞን የመስክ ጉበኝት ለማድረግ ጂንካ ገብቷል። ልኡክ ቡድኑ በዳሰነች ወረዳ የጎርፍ አደጋን ለመከላከል እየተከናወኑ የሚገኙ የወንዝ አመራር ስራዎችን የመገምገም፤ እንዲሁም የመጠጥ ዉሃና ሳኒቴሽን እና የኢነርጂ ፕሮጀክቶች ጉብኝት ይደረጋል። የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ንጋቱ ዳንሳ በጅንካ ኤርፖርት በመገኘት አቀባባል አድርገዋል። በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውኃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ እና የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ በጉብኝቱ ተገኝተዋል።

Share this Post