የበልግ የአየር ንብረት ግምገማ እና የመጪው ክረምት ወቅት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንበያ ዙሪያ ውይይት ተደረገ ፡፡

የበልግ የአየር ንብረት ግምገማ እና የመጪው ክረምት ወቅት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንበያ ዙሪያ ውይይት ተደረገ፡፡ ግንቦት 05/2015(አዳማ ) የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት ባዘጋጀዉ የ2015 ዓ.ም. የበልግ የአየር ንብረት ግምገማ እና የመጪው ክረምት ወቅት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንበያ ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ እንደገለጹት ባለፉት 3 ወራቶች የተሰጠው የአየር ሁኔታ ትንበያ ሲገመገም የተጣጣመ መረጃ መሆኑንና ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ የጎርፍ አደጋ መሰል ተግዳሮቶችን ለመከላከል ብሎም ለመቀነስ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸው፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ህብሰተሰቡ መረጃውን በአግባቡ ከወሰደና ከተጠቀመ ተግዳሮቶችን በተሻለ ሁኔታ መቋቋም እንደሚቻል አስገንዝበዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም ከውሀ፣ ከግብርና፣ ከአደጋ መከላከል፣ ከምክር ቤትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል በዚህ መድረክ አጽንኦት ተሰጥቶት ሊታይ የሚገባው አንደኛው ጉዳይ በቀጣይ ክረምት ወቅት ትንበያ ዙሪያ ሁሉም ሚዲያዎች በተለይ፤ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚያሰራጩ ኤፍ ኤም ራዲዮዎች መረጃውን ተደራሽ ለማድረግ የሚኖራቸው ሚና ላይ መሆን እንደሚገባው እና በአጭር፤ በመካከለኛ በረጂም ጊዜ ኢኒስቲቲዩቱ የሚሰጣቸውን ቅድመ ትንበያዎች ለዜጎች ተዳራሽ እንዲያደርጉ በማሳሰብ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የአየር ጠባይ ክስተቶች በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ሊያሳድሩ የሚችሉትን ተጽዕኖዎች በመከታተልና አስቀድሞ በመተንበይ የደንበኞቻችንና የባለድርሻ አካላትን ፍላጎት ለማርካት በትጋት በመሥራት ላይ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም የበልግ ወቅት የአየር ሁኔታ ትንበያ ትክክለኛነትና ከወቅቱ የአየር ጠባይ ጋር ተያይዘው የተከሰቱትን መልካም አጋጣሚዎችም ሆነ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን በተመለከተ ግምገማ የሚካሄድበትና በቀጣዩ ክረምት ወቅት ሊኖር የሚችለውን የአየር ሁኔታ አስቀድሞ መተንበይ ሊፈጠሩ የሚችሉትን ጎጂ ክስተቶች እንዲሁም መልካም የአየር ሁኔታ አስቀድሞ መተንበይ የሀገራችን ሕዝቦች ተገቢውን ቅድመ-ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል አቅጣጫ የሚጠቁም በመሆኑ በሁሉም ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው የአገልግሎት ዘርፍ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በመድረኩ ኢንስቲትዩቱ በየጊዜው በሀገራችን የተለያዩ ቦታዎች ሊፈጠሩ የሚችሉትን የአየር ሁኔታ ገጽታዎችን አስቀድሞ በመተንበይ የቅድመ-ማስጠንቀቂያና የትንበያ መግለጫዎች የሚሰጥ በመሆኑ ኅብረተሰቡ ይህንኑ መረጃ እንዲጠቀምና የሚሰጠውን የቅድመ-ማስጠንቀቂያ መግለጫዎችን በቅርበት ክትትል እንዲያደርግ ተገልጿል፡፡ በውይይቱ ላይ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲያ አህመድ የውሃ፣ የመስኖ ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና የቋሚ ኮሚቴ አባላት ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የተቋሟት የስራ አመራሮች እና ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

Share this Post