ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በጀርመን ከሚገኘው የሚሲዮኑ ሰራተኞች፣ የልማት አጋር ድርጅቶችና ባለሀብቶች ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡

ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በጀርመን ከሚገኘው የሚሲዮኑ ሰራተኞች፣ የልማት አጋር ድርጅቶችና ባለሀብቶች ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡ መጋቢት /2015 ዓ/ም፡ በጀርመን በርሊን ሲካሄድ በነበረው 9ኛው የበርሊን ሃይል ሽግግር ጉባኤ (Berlin Energy Transistion Dialogue – BETD – 23) ተሳትፎ ያደረጉት የውኃና ኢነርጂ ሚንስትሩ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በጀርመን ከሚገኘው የሚሲዮኑ ሰራተኞች እና የልማት አጋር ድርጅቶች ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡ የውኃና ኢነርጂ ሚንስትሩ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በጀርመን በርሊን በሚገኘው የኢትዮጵያ ሚሲዮን ሰራተኞች ጋር በአሁናዊ ሀገራዊ ጉዳይና የአጋር ድርጅቶችን ትብብር በሚጠይቁ የመሰረተ ልማት ፕሮግራሞች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አደርገዋል፡፡ በሚሲዮኑ ልዮ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍቃዱ በየነን ጨምሮ፤ ምክትል የሚሲዮኑ መሪዎች፣ ዲፕሎማቶችና ኦፊሰሮችን ያካተተው ውይይት፣ በልማት ፕሮግራሞች፣ አሁናዊው የሀገራችን ሁኔታ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የተደረገውን እርቀ ሰላም ተከትሎ በመንግስት በኩል እየተደረ ስላለው የሰብአዊ ድጋፍና የመልሶ ማልማት እንቅስቃሴ፣ ከድርቁና ተያያዥ ተግዳሮቶች ፣ ሀገራችን በእነዚህ ችግሮች ውስጥም ሆና እያከናወነቻቸው ስላለችው ሰፋፊ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታ ሂደትን አስመልክቶ ማብራራያዎችን ሰጥተዋል፡፡ በተመሳሳይ ከአፍሪካ ፈራይን (Afrika - Verine) በተባለ በጀርመን የቢዝነስ የግሉ ዘርፍ ካምፓኒዎች ማህበራት ማስተባበሪያ በኩል ከባለሀብቶች ጋር በአካልና በበይነ መረብ በኢትዮጵያ በኢነርጂ ዘርፍ ስላለው የኢንቨሰትመንት አማራጮችን አስመልክተው ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን ከተሳታፊዎቹ ለተነሳላቸው ጥያቄዎችም ጭምር ምላሾችን ሰጥተዋል፡፡ በተለይ ኢትዮጵያ ካላት አማራጭና የታዳሽ ሃይል ዘርፍ እምቅ አቅም ልክ ተጠቃሚ አለመሆኗን ገልጸው ድርጅቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው መዋዕለ ንዋያቸውን ቢያፈሱ ተጠቃሚ ከመሆናቸውም በላይ ለኢትዮጵያውያን በርካታ የሥራ ዕድል መፍጠር እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡

Share this Post