ቀጠናዊ የሀይል ግብይት በአፍሪካ ሀገራት መካከል ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ጠቃሚ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ቀጠናዊ የሀይል ግብይት በአፍሪካ ሀገራት መካከል ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ጠቃሚ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ጥር 2016 ዓ.ም. ( ው.ኢ.ሚ) እ.ኤ.አ ከጥር 31 እስከ የካቲት 1/ 2024 በአሩሻ ታንዛንያ በተካሄደው አምሰተኛው የታንዛንያ ኢነርጂ ትብብር ሰሚት ላይ የተካፈሉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ በመደረኩ ባደረጉት ገለጻ ቀጠናዊ የሀይል ግብይት በአፍሪካ ሀገራት መካከል ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በማብራሪያቸው አክለው ቀጠናዊ የሀይል ግብይት የታዳሽ ሀይል ኢነርጂ ቁጠባ ከማበረታታት ባሻገር፤ የጋራ የኤሌክትሪክ ገበያ ለመፍጠር እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡

የኢነርጂ ልማት ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ስለሚጠይቅ፤ እንደሃገር የግሉ ዘርፍ በታዳሽ ሀይል ልማት እንዲሰማራ ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን አንስተው፤ የኢነርጂ ሴክተር ሪፎርም፣ የኢንቨስትመንት አዋጅ እና የመንግስትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት የሚያበረታታ ህጋዊ ማእቀፍ መዘጋጀቱ የግሉ ዘርፍ በሀይል ልማት ኢንቨስትመንት እንዲሰማራ አስቻይ ሁኔታች መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ቀጠናዊ የሀይል ትስስሩን ለማሳደግ እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡

Share this Post