የትንሳኤ እና የኢድ-አልፈጥር በዓላትን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሃግብር ተካሄደ።

የትንሳኤ እና የኢድ-አልፈጥር በዓላትን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሃግብር ተካሄደ። ሚያዝያ 05/2015 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የትንሳኤ እና የኢድ-አልፈጥር በዓላትን ምክንያት በማድረግ 350 ለሚሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የተቋሙ ሰራተኞች ከ900 ሺ ብር በላይ ወጪ በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሃግብር አካሄደ። በማእድ ማጋራት መርሃግብሩ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በበዓል ወቅት መሰል ተግባራት ሲከናወን የመጀመሪያ እንዳልሆነ ገልፀው እንደአንድ ቤተሰብ አብሮ ማእድ መጋራት ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን የሚያጠናክር በመሆኑ በበዓል ወቅት ያለውን ተካፍሎ መብላት መለመድና ባህል ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ አያይዘውም እንደሚኒስቴር መስሪያ ቤት በዓልን በዚህ መልኩ ስናከብር ያለንን በማካፈልና ለሌሎች ምሳሌ በመሆን ተካፍሎ የመብላት ባህላችንን ለማጠናከርና ካለን ላይ መስጠትን ለማለማመድ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዕለቱ ካፒታል ሆቴልና ስፓ በመርሃግብሩ ላይ ሻይ ቡና በማቅረብ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጎን መሆኑን የገለፀ ሲሆን ሰራተኞቹም ሚኒስቴር መ/ቤቱ ስላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

Share this Post